Kinijitswiss.org contact us
Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org
 


 
main content

የቅንጅት ድጋፍ ድርጅት በስዊዘርላንድ

አመሰራረት:

በሃገር ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የአራት የፖለቲካ ድርጅቶች ውህደት ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲን መፍጠሩ ይታወቃል:: በዚህም መሰረት:

  • = ቀድሞ በተናጠል ይንቀሳቀሱ የነበሩ የነዚሁ አራት የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ አባላት፣
  • = በሃገር ውስጥ ያለው አፈናና የቅልበሳ ሁኔታ እንዲሁም የሀገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ በእጅጉ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን፣
  • = የተጀመረው የዲሞክራሲ ሂደት እንዳይስተጓጎልና «የግለሰብ ነፃነት ይቅደም፣ የሕዝብ ድምፅ ይከበር » የሚለውን የቅንጅትን ጥሪ በሙሉ ልብ የተቀበሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ

በአንድ ላይ በመሆን ተሰባስበው ጃንዋሪ 14 ቀን 2006 አመተምህረት የቅንጅት ድጋፍ ድርጅትን በካንቶን ዙሪክ ቫሊሰለን Wallisellen ከተማ መሰረቱ::

የድጋፍ ድርጅቱ ከተቋቋመበት አላማዎች ዋና ዋናዎቹ :

በሃገር ቤት የተካሄደውን እና እስካሁንም የዘለቀውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች እስራት፣ ወከባ ማጋለጥና ለአለም ህዝብ ማሳወቅ: በዚሁም መሰረት በሀሰት ክስ ተወንጅለው የታሰሩት መሪዎቻችንና ደጋፊዎቻቸው፣ እንዲሁም የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክና የሙያ ማህበራት መሪዎች እንዲሁም የሕሊና እስረኞች የሆኑ ሁሉ እንዲፈቱ በሚቻለው መንገድ ሁሉ በመጠቀም አለም አቀፍ ጫናን መፍጠር፣


በተመሳሳይ መንገድ ከተቋቋሙ የድጋፍ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የህዝቡ የነፃነት ትግል እንዳይዳፈን ያለማቋረጥ የጋራ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ፣

የሰው ልጆች መብት የሚከበርባት የሕግ የበላይነት የሚረጋገጥባት ዲሞክራሲ የሰፈነባት አንድነቷና ሉአላዊነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ትግል በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በቅንጅት ዙሪያ ማሳተፍና ማንቀሳቀስ፣

በሃገር ቤት በሚደርስበት የፖለቲካ ጫና የተነሳ ሃገሩን ለቆ ለተሰደደው ስደተኛ ችግሩን ትኩረት ሰጥቶ በመከታተል የተቃውሞ አቤቱታዎችና ሰልፎች በማዘጋጀት፣ በመሳተፍ የስደተኛውን ቅሬታና አቤቱታ ለባለስልጣናት ማሳወቅ፣ በደልና ግፍ የተፈፀመባቸውን መርዳትና መደገፍ ይገኙበታል::

የድጋፍ ድርጅቱ አሁን ያለበት ሁኔታ:

የቅንጅት ድጋፍ ድርጅት በስዊዘርላንድ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ከላይ በተዘረዘሩት አላማዎች ዙርያ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፣ በማከናወንም ላይ ይገኛል:: የድጋፍ ድርጅቱ ቤልጅየም ሉቨን ከተማ በተደረገው ስብሰባ በመሳተፍ በአህጉር ደረጃ በተቋቋመው የአውሮፓ ካውንስል ውስጥም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል::

ወገናዊ ጥሪ:

ቅንጅት አንግቦት ለተነሳውና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከኋላው ለተሰለፉለት የቅንጅት ራእይ መሳካት በሚደረገው ርብርቦሽ እርስዎም እንዲሳተፉ የቅንጅት ድጋፍ ድርጅት በስዊዘርላንድ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል:: ይፃፉልን ወይም ይደውሉልን:: ለግንኙነት በሚከተሉት አድራሻዎች ይጠቀሙ::

አድራሻ :
KINIJIT Support organization in Switzerland
Postfach 1124 , 8152 Opfikon, SWITZERLAND
ስልክ :
0041 79 207 92 07
ፋክስ :
0041 811 08 09
ኢሜይል :
kinijitch@yahoo.com
ዌብ ሳይት :
www.kinijitswiss.org


 

 
`

@2007 - KINIJIT Support Organization In Switzerland Web Design By SaNet