Kinijitswiss.org contact us
Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org
 


 
main content

አንድ ሴኮንድ
(አንዱአለም - ከስዊዝ)

እንፈርዳለን አሉ - እንዳኛለን አሉ
ለአፍ ቀሎ ቃሉ
ካባ ቢደርቡ የሆኑ መስሏቸው
ክቡሩ ዳኝነት ረክሶ በሆዳቸው
ስሙን ቢታደሉት ጊዜ ፈቅዶላቸው
ቋት አራች እንዲሉ ..
....አይነጋ መስሏቸው
የፈራጆች ፈራጅ ቁልቁል እያያቸው
ከሕዝብ አብራክ ወጥተው
በክቡሩ ቦታ በተቋማት ኖረው
. አንቱታን ተችረው
ቅዱስ መፅሐፉን ቅዱስ ቁራኑን
.በእጃቸው ይዘው
በሃቅ ሊሰሩ ለፍትሕ ዘብ ቆመው
በሐሰት ላይፈርዱ ምለው ተገዝተው
ታድያ ምን ነካቸው?
የማሉለት መፃፍ እንዴት ያደርጋቸው?
ያጠለቁት ካባ እንዴት ያፍርባቸው!
ደሃን በእራፊ በሆዱ ደልለው
የማሉለትን ቃል .
እነሱ እንደካዱ እሱንም ካድ ብለው
በናትህም ቢሆን ባሰት መስክር ብለው
በወለደች እናት በሴት ልጅ ጨክነው
ድርስ ነፍሰጡርን እስርቤት ወርውረው
አለሙን ባላየ በሽሉም ጨክነው
በምጧ አፊዘው እስርቤት ገላግለው
.እንዴት አስቻላቸው?!
አትግደሉ ያለን ሰው ገለሃል ብለው
ሃገር ትቅና ያለን ሃገር ካድክ ብለው
... ባይገባቸው እንጂ
መላው ኢትዮጵያዊን ወንጀለኛ አድርገው
ሰው ሳይሆን ፍትሕን
ጨቅላ ዲሞክራሲን እችሎት አቁመው

.. ሊያስሩ መፍጠናቸው
ወዴት ነው ሩጫው የት ነው መቆሚያቸው?
ለሆድ ነው ለህሊና .

... መማር መድከማቸው !?
ፈራጅ አፋራጁም .
.. አንድ ሆኖ ስራቸው አበቃቀላቸው
አሁንስ አዘንኩኝ ተጨነቅኩላቸው
በምድር ከሰው ጋር
... መኖር አቅቷቸው
እላይም ባምላክ ዘንድ

.. ከፍቶ ቅጣታቸው
ውስጣችን ከሚያዝን ባወዳደቃቸው
እነሱ ሲጠሉን እኛ አንጥላቸው
እነሱን አንሁን ፍቅር እንስጣቸው
ህሊናን ቆልፎ ዘግቶ ከያዛቸው
ካበደነ ህመም የቀን እንቅልፋቸው
ምናልባት ቢነቁ ሰው መሆን ገብቷቸው
የመጥላት በሽታን ነቅሎ ከልባቸው
በቦታው ፍቅርን እንዲተካላቸው
ሃገራዊ ፍቅር እንዲያበቅልባቸው
ልቦናውን ሰጥቶ ሰው እንዲያረጋቸው

ፈጣሪ ሃያል ነው .!
እንደ እምነታችን
.... ዝም አንበላቸው
ወገን እውነቴን ነው
በቀን አንድ ሴኮንድ... እንፀልይላቸው::

 


 
`

@2007 - KINIJIT Support Organization In Switzerland Web Design By SaNet