Kinijitswiss.org contact us
Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org
 


 
main content

 

« ከገባቸው! ..እስኪገባቸው!
በቅኔም እናውራቸው »

(አንዱአለም - ው - ስዊዝ - (andualem19@yahoo.com)

ለንቦቹ

ዝንብ እንደንብ
ጠጅ ድሮ ቀረ - ዘንድሮ የት አለ፣
ማሩንስ ማን ይስራው - ቀፎ ባዶ ዋለ፣
ስኳር ላሽ ዝንብ ሁሉ .
... ንብ ካልሆንኩ እያለ::

 

ሁሉ አማረሽ
አራሹም ማረሱ ማምረት ሳይቸግረው፣
ነጋዴም ማቅረቡ ማዳረስ ሳይከብደው፣
ሁሉ አማረሽ ሆኖ አስቸገረ ገዢው::

ቁርጥ
ካቻምናን ገፋነው - በጎመን ከጓሮ፣
አምናም እንደዋዛ - አለፈ በሽሮ ፣
እያማረን አንቅር - እንይ ተቀይሮ
ቢላችንን እንሳል - አያሻም ቀጠሮ፣
ወይፈኑን እንጣለው - ቁርጥ ይሁን ዘንድሮ::

 

 

ከንቱ እርሻ
ላይሆናቸው እርሻ ቆፍረው ቆፍረው፣
ቆላውን ከደጋው እንለየው ብለው፣
የተከሉት ጫጨ ጨነገፈባቸው፣
አልወገድ ብሎ የዘር ችግራቸው::

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


 
`

@2007 - KINIJIT Support Organization In Switzerland Web Design By SaNet