ይድረስ
ለሴቶች እህቶቼ
!
ሀና
ተረፈ ( አራው
- ስዊትዘርላንድ
)
ጨለማውን
ከማውገዝ ይልቅ
በእጃችን
ያለውን ሻማ
ማብራቱ የበለጠ
ውጤታማ ያደርገናል
!
ሁሉም
ሰው ይጋራዋል
ብዬ እንደማምነው
እና እኔም ያለምንም
ማመንታት እንደምስማማው
የእናት ፍቅር
በቃላት ሊገለጽ
ከሚገባው በላይ
እጅግ ስር የሰደደ
ነው። እጅግ
እጅግ
በጣም! ለዚህም
ነው በእናት
የሚመሰሉ ነገሮች
ሁሉ በውስጣችን
የጠለቀ ስሜትን
ያጭራሉ::
ሀገራችን
ኢትዮጵያም
ይሕው የእናትነት
ፍቅሯ እውስጣችን
ተቀብሮ ስላለ
ደስታዋ ይናፍቀናል
ተድላዋን እንመኛለን፤
የዛኑም ያህል
ሀዘኟ ያሳዝነናል፤
ችግርዋ አንገታችንን
ያስደፋናል፤
የሚደርስባት
ክፉ ነገር ሁሉ
እጅግ ያስቆጣናል
እረፍት ይነሳናል(
ለእናት ባለን
ፍቅር መጠን)።
ነገር ግን ይህ
ሁሉ ቁጣ ወይም
እንቅልፍ ማጣት
እንዲሁም ችግሯን
ለመቅረፍ እንደ
አቅማችን የምናደርገው
ጥረት እምን
ድረስ ነው?
የሚለው እጅግ
ወሳኝ ጥያቄ
ነው።
እንዲህ
እንደ እናት
የምንንሰፈሰፍላት
ሀገራችን ከቀደምት
ባለታሪክነትዋ
ከተፈጥሮ ባለሀብትነትዋ
እንዲሁም የጥቁሮች
ኩራት በመባል
በጀግንነት
እየታወቀች
ብትኖርም ከዚሁ
ባልተናነስ
ሁኔታ ከሶስተኛው
አለም ጋር የምትጠቀምስበት
የብልሹ አስተዳደር
እና የድህነትዋ
ጉዳይ መቅረፍ
እጅግ ናፍቆት
እየሆነ መጥትዋል።
በተለይ አለም
እየተለወጠ
እና የሰው ልጅ
ህሊናም እጅግ
እያደገ በመጣበት
በዚህ ዘመን
የኛ መሪዎች
ለሆዳቸው
እና ለጊዚያዊ
ጥቅማቸው ብቻ
በማሰብ ከአለም
እድገት በተጻራሪው
ቁልቁል እየተንደረደሩ
መሆናቸውን
ስናስተውል
እምንናፍቀውን
በጎ ነገር ሁሉ
በፍጹም የማንደርስበት
ያስመስለዋል።
ለውጥ
ሁልጊዜም ቢሆን
በትግልና በጠንካራ
ጥረት የሚመጣ
ነው፤ ትግል
ደግሞ መራራና
እልህ አስጨራሽ
ነው ፤ በተለይ
እንደ ኢትዮጵያ
ባሉ ደሃና ከላይ
የጠቀስኩዋቸው
መሪዎች ባሉበት
ምሬቱ ከባድ
ነው። ውጤቱ
ግን ተቃራኒ
ነው።
እንደ
ዋዛ ሁሉት አመቱን
እያሳለፈ ያለው
የአገራችን
የግንቦት 97
ቱ ምርጫና ውጤቱ
በዚህ ረገድ
ብዙ ነገሮችን
አስተምሮናል
አያስተማረንም
እዚህ ደረጃ
ደርሶዋል።
"ለእነርሱ"
ለአምባገነኖቹ
፤ አለም ሲፈጥን
ጭራሽ በደንብ
በመተኛት ላይ
ላሉት "ለእነርሱ"
ግን ስራቸውን
የጨረሱ መስሎዋቸው
ይሆናል። እኛ
ግን ገና አዲሱ
የትግል ሜዳ
ውስጥ መግባታችን
ነው።በተለይ
ወደ ሰለጠነው
አገር የእድሜያቸውን
ግማሽ በላይ
በመመላለስ
ሲልም በመኖር
ሆዳቸውን በመሙላትና
ፎቶ ብቻ በመነሳት
እንደሚመጡት
እንደ ህሊና
ቢሶች መሪዎች
ሳይሆን ከኖሩበት
ስልጡን አካሄድን
ባሳዩን በሳል
መሪዎቻችን
ንድፍና ለአዲሱ
የሰላማዊ ትግል
ሜዳ ፍጹም አዲስ
ነን እና ትግሉ
ገና ገና
አልተጀመረም።
እና
የጽሁፌ ነጥብ
የሆነውም በዚህ
አዲስ የትግል
ሜዳ ውስጥ እኛ
ሴቶችበተለይ
" አሁን" የቱ ጋ
ነን የሚለው
ነው። ወሳኝ
በሆነው ስዓት
ላይ የነበረው
የሴቶቻችን
ተጋድሎ እና
አርአያነት
እንደ ታሪክ
ተወርቶ የሚያልፍ
ሳይሆን ሁላችንንም
ለበለጠ ትግልና
ስራ የሚያነሳሳ
መሆን አለበት።
ከግማሽ በላይ
የእርግዝና
ጊዜዋን በእስር
አሳልፋ እዛው
የተገላገለችው
ጋዜጠኛ ሰርካለም፤
የ48 አመትዋ
መምህርት ወ/ሮ
ንግስት ገ/ህይወት
፤ ከዝዋይ ማጎሪያ
ጨምሮ በአዲስ
አበባ እስር
ቤቶች ብዙ ጊዜን
ያሳለፉት የ
52 አመትዋና
የ 5 ልጆች እናት
የሆኑት ወ/ሮ
ሙሉነሽ አበባየሁ
እንዲሁም ህሊናዬን
ሽጨ በዜጎች
ላይ አለአግባብ
አልፈርድም
ብላ ለኢህአዲግ
ከፍተኛ ራስ
ምታት የሆነችው
ቆራጧ የህግ
ባለሙያ ወ/ሮ
ብርቱካን ሚደቅሳ
. ወ ዘ ተ የከፈሉትና
እየከፈሉት
ያሉት መስዋዕትነት
" እኛስ አሁን
ምን እያደረግን
ነው ? " በሚል
እንቅልፍ ሊነሳን
ይገባል።
ሴቶች
በተፈጥሮ ብልህ
ናቸው ፤ መለኛ
ናቸው፤ ነገሮችን
ለመለወጥ አይነተኛ
መሳሪያ ናቸው
የሚባለው ያለምክንያት
አይደለም።
በተለይም አሁን
በገባንበት
የስላማዊ የትግል
ሜዳ ውስጥ ራሳችንን
ለአደጋ ሳናጋልጥ
ልንሰራ የሚገቡን
በርካታ ስራዎች
አሉ። በየእድሩ
፤ በየት/ቤቶች
፤ በገበያ ቦታዎች
እና መሰባሰብን
በሚፈጥሩ ማንኛውም
አጋጣሚዎች
መወያየት እና
ኢህአዲግ ለእድሜ
ማራዘሚያነት
እየተጠቀመበት
ያለውን በዘር
በሀይማኖት
የመለያየት
ሴራ በጥሰን
የበለጠ እጅ
ለእጅ በመያያዝ
ትግሉን አንድ
እርምጃ ማራመድ
ይጠበቅብናል
። ሶስት እና
አራት ሆነን
በምንገኝበት ትንሽ አጋጣሚ
ሁሉ ለደቂቃዎች
ስለ ሀገር እና
ወቅታዊ ሁኔታዎች
መነጋገራችን
በጊዜ ብዛት
ድንጋይን እንደሚሰብር
የውሃ ጠብታ
አቅም ይፈጥራል
እና ልናስብባት
ግድ ይለናል።
ህወሃት/ኢህአዲግ
በባህሪው እንደሚታወቀው
አንድነትን
በፍጹም አይወድም/
አይፈልግም
/ ለዚህም በብዙ
አቅጣጫ ህዝባችን
ለመከፋፈል
ብዙ ርቀት ሄድዋል
ባይሳካላትም
። እኛ ደግሞ
" አንድነታችን
ልዩ መለያችን
ነው በፍጹም
አንክፋፍልም"
ብለናል። ይህ
በሳል የትግል
ስልት ደግሞ
ለዚህ አቛማችን
መመዘኛ ፈተና
ሆኖ ነው የቀረበው
ምክንያቱም
ሰላማዊ ትግል
ውስጥ ያለው
ዋናው ህዝባዊ
እምቢተኛነት
ተግባራዊ የሚሆነው
ፍጹም አንድ
ስንሆን ብቻ
ነው ፤ ለዚህ
በጣም ቀላል
ምሳሌ ለመጥቀስ
ከምርጫው ማግስት
በሁዋላ በነበሩ
ክስተቶች የአ.አ
ታክሲ አሽከርካሪዎች
በአንዲት ጀምበር
የወሰዱት የአንድነት
እርምጃ ከበቂ
በላይ የቅርብ
ትዝታ ነው።
እናም
ውድ አኢትዮጵያውያን
እህቶቼ በያላችሁበት
ወሳኝ ከሆነው
በዚህ ወቅት
ላይ ይበልጥ
እጅ ለእጅ ልንያያዝ
ይገባናል።
ትግሉ ተጀምሯል
ጎህ እየቀደደ
ነው ጎህ ሲቀድ/
ሲነጋጋ/ መልሶ
የሚወስድ እንቅልፍ
ደግሞ እጅግ
ከባድ ነው የቀኑን
የስራ ውሎአችንን
ሁሉ ክፉኛ የሚያበላሽ
ነው። እና መልስን
ሳንተኛ እንደነቃን
ስራችንን እንቀጥል።
የትኛውም ሀይማኖት
ተከታይ ብንሆን
እውነት እላችሁዋለሁ
አምባገነኖችን
/ጨቛኞችን/
መታገል እና
ለህዝብ ነጻነት
መስራት ለአምላክ
መታዘዝ ነው
እና ይበልጥ
እጅ ለእጅ በመያያዝ
በቀሪው እድሜያችን
ክብር ያለው
ስራ ሰርተን
እንለፍ። ስለአኛ
እንደ ሻማ እየቀለጡ
ያሉትን በእስር
የሚሰቃዩትን
መሪዎች በጎ
ስራ ጫፍ እናድርሰው።
የሞቱትን ሰማዕታት
አጽም እንዳይወቅሰን
እንሁን። አሁን
የቱ ጋር ነን
ብለን ራሳችንን
እንጠይቅ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን
ይባርካት