ሚናችሁን
ለዩ !
የትግሉ
ማዕበል፣ መርከቡን
ሲንጠው
ዋይታና ጫጫታ፣
ምድርን ሲያናውጠው
ከጎንህ
ሲወድቅ፣ ደጀኔ ነው
ያልከው
እንግልት
ሲበዛ፣ ሲጠና መከራው
ያኔ ነው
የሚለየው፣ ፍሬና
ገለባው
ወላዋይ
ሲዳዳ፣ ከትግል ግብ
ግብ
የመሐል
ሰፋሪው፣ መሹለኪያውን
ሲያስብ
ቁርጠኛው
ሲቀጥል፣ ፈሪው
ሲንጠባጠብ
እንዲያ
እየሆነ ነው፣ ወትሮም
ትግል እንጅ
መች ዳር
ደርሶ ያውቃል፣
በሹምባሽ ወዳጅ
ታጋይ
አይፈታም ባድር
ባዮችና በልፍስፍሶቹ
በነሆድ አደሩ
በከዳተኞቹ
በእነ የወሬ
ቋት፣ በነአቶ
አይሰለቹ
የባንዳ
አቀንቃኞች
ተለጣፊዎቹ
ኢዴፓ
ነኝ አሉ ? ክህደቱ
ባያሌው
በከንቲባው
ቢሮ፣ አይናቸውን ተክለው
ነጋን
አሳስሮ፣ ሊበላ
የቋመጠው
እርሱን
አያድርገኝ፣ ወያኔ ሲጠፋ
የትም
አያደርሰው፣ የባንዳ
ልጠፋ
ተባባሪ
የሆነ፣ አገር ስትጠፋ
ብድሩን
ይከፍላል፣ ከማንም
በከፋ
ተው ወገኔ ስማ፣
ልብህ አያመንታ
ያድን
የመሰለህ፣ አጥብቆ
ዝምታ
ሚናህን
ያልለየህ፣ ዙርያህ
የተምታታ
አፍህና ልብህ፣
የማይሄድ በተርታ
ቁብም
የማይሰጥህ፣ ያገርህ
ውለታ
ላንተስ ማን
እንዲያዝን፣ አብረህ
ብትመታ ?
ቅንቅን
የጀርባ እከክ፣
ወላዋይ ተባዩ
ተለጣፊ
ባንዳ፣ አድርባይ
ሰላዩ
አያገባኝም
ባይ፣ ዳር ሆነው
የሚያዩ
አረንጓዴ
ቢጫው፣ ባንዲራችን
ቀዩ
ሰይፉ
እንዳይበላችሁ፣
ሚናችሁን ለዩ
( Mail Box )
|