የምርጫ ነገር / ክፍል አንድ /
በአውሮፓው
ክፍለ አለም ጠንካራ
ከሚባሉት የቅንጅት
ድጋፍ ድርጅቶች ውስጥ
አንዱ የሆነው
የቅንጅት ድጋፍ
ድርጅት በስዊትዘርላንድ
በመጪው ፌብሩዋሪ
አልያም ማርች ውስጥ
ሁለተኛውን አጠቃላይ
ጉባኤውን ያካሄዳል
፡፡ ከአጠቃላይ
ጉባኤው አጀንዳዎች
ውስጥ አብዩ የድርጅቱ
ተግባር አመራር ኮሜቴ
ምርጫ ነው፡፡ በዚሁ
የአጠቃላይ ጉባኤ
ጉዳይ ላይ ከአንድ
ወዳጄ ጋር ስንጨዋወት
ጉባኤው
የምንፈልገውን
አይነት አንድነቱን
የጠበቀ ድርጅት፣
ንቁና የሚታገሉለትን
አላማ ጠንቅቀው
የሚረዱ አባላት ዳግም
ይወልድ ዘንድ ምን
ሊደረግ እንደሚገባ
አንዱን ሀሳብ ስንጥል
አንዱን ስናወርድ
እንደው የድጋፍ
ድርጅቱን አባላት
በጉዳዩ ላይ እንዲወያዩና
በንቃት በምርጫው
እንዲሳተፉ ከወዲሁ
ፍላጎት የሚያነሳሱ ውይይቶችን
መክፈት አንድ ነገር
እንደሆነ ተስማማን
፡፡ ይህም ጽሁፍ ዲሞክራሲያዊ
ምርጫን ለማበረታት
በተለይም የውይይትን
ልማድ ለማሳደግ
የበኩልን ከማድረግ
አንጻር ቀርቧል፡፡
ምረጡኝ
ላገልግል
ከረጅም ጊዜ
በፊት በተመለከትኩት
አንድ አሜሪካዊ ፊልም
ውስጥ በአንድ አንደኛ
ደረጃ ት/ቤት ውስጥ
ለሚደረግ የተማሪዎች
ም/ቤት ምርጫ / Student Council /ዝግጅት
የሚያደርግ አንድ
ወጣት በየእለቱ ምሽት
ላይ ከወላጆቹ ጋር
የምርጫ ንግግር
ዝግጅት ያደርጋል፡፡
ወላጆቹም ሙሉ ሀሳባቸውን
የልጃቸው የምርጫ
ዝግጅት ላይ አድርገው
አንዳንዴም በናሙና
የምረጡኝ ክርክር
አባት ተፎካካሪ
ተወዳዳሪ እየሆነ ሁሉ
ትዕይንቱ እንዲህ
እንዲህ እያለ ይቀጥላል
፡፡ በየትኛውም ደረጃ
በሚገኝ የህይወታችን
ህዝባዊ ገጽታ የመሪነት
አልያም
አስተባባሪነት
ሀላፊነትን መረከብ
ከስነ ልቦናዊም ይሁን
ማህበራዊ ገጹ
ብንመለከተው ብዙ
ጠቃሚ አንድምታ
ይኖረዋል ፡፡ ሰው
ማህበራዊ ፍጡር
እንደመሆኑ በሰዎች
ዘንድ ተቀባይነትን
ማግኘት እንዲህ ቀላል
የሚባል የህይወት
ነገር አይሆንም ፡፡ ብዙዎቻችን
በምናውቀው
የምዕራባዊያኑ
የፍላጎቶች ሰንሰለት /
Hirearchy of needs / የሚበላ የሚጠጣ
ከሞላ በኋላ የሰው
ልጅ ቀሪው ድካሙ
በሰዎች ዘንድ
ተቀባይነት ለማግኘት
የሚደረግ ጭንቅ ጥብ
ነው ፡፡ የፓለቲካ
ምርጫ በስዎች
ተቀባይነት ከማግኘት
ሌላ ተጨማሪ እንደ
ገንዘብ ፣ የሀይል
የበላይነት ፍላጎት / power
intrests / ፍላጎቶችን
የሚያካትት ቢሆንም
እነርሱም ቢሆኑ ሰብዐዊ
ፍላጎቶች ናቸውና
በማናቸውም
የፓለቲካው መዋቅር
ደረጃዎች ያሉ ሰዎች
ይህ የሃላፊነት ቦታን
ለመውሰድ እመጥናለሁ
ብሎ መነሳት በራሱ ጀግንነት
ነው ፡፡
በኢትዮጵያውያንም
ዘንድ ጉዳዩን
የተመለከትነው
እንደሆን ከላይ
የተነሱት ሰብአዊ
ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎቶች
መኖራቸው
የማይጠረጠር ቢሆንም
እነዚህን ፍላጎቶች
ከዳር ለማድረስ የምንጠቀምበት
ባህል/ ልማድ ግን
ነቀርሳ የተጣባው
አይነት ነው፡፡ በት/ቤት
ሳለን የክፍል አለቃ
መምረጥ ከጀመርንበት
ጊዜ አንስቶ እስከአሁን
ድረስ እኔ ልመረጥ ፣
ላገልግላችሁ
ችሎታውና ፍላጎቱ
አለኝ ማለትን
የምንሰማው እምብዛም
ነው፡፡ ት/ ቤት ሳለን
ጎበዙ ተማሪ
የሚፈለገው ሰኔ 30 ቀን
ለሽልማት ብቻ ነው፡፡
ሌሎች የእድሜ እኩዮቻቸውን
አስተባብረው
ከፈለጉበት ማድረስ
የሚችሉ የልጅነት
መሪዎች እንዃ
የሚፈለጉት ወይ ከሌላ
ት/ቤት ተማሪዎች ጋር
ጸብ ሲኖር አልያም ከተማ
ውስጥ የጀብድ ስራ
ለመስራት ስንፈልግ
እንዲመሩን ነው፡፡ አስተማሪው
ጉልበተኛና በዕድሜ
ከሁላችን ከፍ
የሚለውን ተማሪ
የክፍል አለቃ አድርጉ
ይሾመዋል፣ ከዚያም
እርሱም በረባ
ባልረባው ፍዳችንን
ያሳየናል - አንድ ቀን
የአንዱን ጥርስ
አውልቆ ከሹመቱ
እስኪሻር ድረስ ፡፡
በከፍተኛው
የፓርቲ ፓለቲካ
መዋቅር ማለትም
በብሄራዊ ምርጫ ካልሆነ
በቀር በተቀሩት ሌሎች
ማህበራዊ ፣
ሃይማኖታዊና
ኢኮኖሚያዊ ስብስቦች
ምረጡኝ ችሎታው አለኝ
ማለት በእኛ
ማህበረሰብ ነውር / taboo/ ነው
፡፡ በነዚህ የሰዎች
ስብስቦች / እድር
እንበል ፣ እቁብ ፣
ሰበካ ጉባኤ ይሁን
የአጥቢያ
ቤተክርስትያን ቦርድ
፣ የሰራተኛ ማህበር
ይሁን የንግድ ም/ቤት /
እልፍ ወገኖቻችን
በመሪነት የማገልገል ፍላጎቶቻቸውን
እፍን አድርገው
እያዳፈኑ፣ የተጠቆመ
እየመረጡ ከምርጫው
አዳራሽ እንኳ ሳይወጡ
ተመራጮቹን እያማረሩ
አሉባልታ እያኘኩ ወደየቤቶቻቸው
ይከተታሉ፡፡
እኛም
ጋር ምርጫ ከመጣ
እንግዲህ ምረጡኝ
ላገልግል የሚል አንድ
ደፋርና ሀቀኛ ሰው
እናገኝ ይሆን?
ወይንስ ሌሎች ይጩኝ
፣ ሌሎች ችሎታዬን
ደርድረው አሞግሰውኝ
ሲያበቁ እንዲያውም
ለይምሰል ያህል / እኔ
ብዙ ስራ
አለብኝ ብትችሉ ከእኔ
የተሻሉ ብዙዎች አሉ
እነርሱን ምረጡ/ እያለ
የአደባባይ ትርዒት የሚተውን?
በበኩሌ እጅግ ብዙ
ችሎታው ያላቸው፣
የሀገርም ነገር
የሚያንገበግባቸው
ኢትዮጵያውያን
በተለያዩ አጋጣሚዎች ላይ
ተዋውቄያለሁ ወዲያውም
በአስተሳሰባቸውም
በስነ ምግባራቸውም
በግሌ ለዚህኛው ወይም
ለዚያኛው ሃላፊነት
እያልኩ
አጭቼያቸዋለሁ፡፡
የሀገር
ነገር ከተባለ የግልና
የቤተሰብ
ህይወታቸውን ሳይቀር
ሁለተኛ ደረጃ
የሚያስይዙ፣ ቅንጅት
እንዲህ ሆነ እስቲ
ኪሳችሁን ዳብሱ ሲባል
ለጥሪታቸው እንዃን
የማይሳሱ፣ የተለያዩ
ስብሰባዎችንና
ውይይቶችን
ለማስተባበር
የኑሮዋቸውን መሰረት
የሆነውን ስራቸውን ሳይቀር
እያወኩ ከስሜን ደቡብ
ህዝብ ለማስተባበር
የሚሮጡ፣ በተገኙበት
ውይይት መድረክ ሁሉ
ከእውነት ውጪ ፈቀቅ
የማይሉ የመርሆ ስዎች፣
የተለያዩ በትምህርትና
ስልጠና ያገኙዋቸውን
ተስጥኦዎች
ለኢትዮጵያ ነገር
ሲባል እንዲሁ በነጻ
በተገኘው ጊዜ ሁሉ የሚያበረክቱ፣
ብቻ ለቅንጅትም ይሁን
ድርጅቱ ይዞ
ለተነሳቸው አላማዎች
ሲሉ ብዙ ሊሰጡ ነግር
ግን ትንሽ ሊቀበሉ / ያውም
በስኬት እርካታ የሆነ
እንደሆን / የተዘጋጁ
! እንግዲህ
እነዚህ ሁሉ ቢያንስ
ቢያንስ እኔ ድርጅቱን
ለማገልገል ፈቃደኛ
ነኝ ይሉ ዘንድ
እመኛለሁ፡፡ እራስን
ለህዝብ አገልግሎት
ማቅረብ ጀግንነት
ስለሆነ ይልቅም
የዲሞክራሲ አካሄድ
ከስር ወደ ላይ ይሆን
ዘንድ
በየአካባቢያችን
ያሉትን የሲቪክና
የፓለቲካ ድርጅቶች
በዚሁ ቅኝት መቃኘት
የቅድሚያዎች ሁሉ
ቅድሚያ ስለሚሆን
ምረጡኝ ላገልግላችሁ
ለሚል ቢያንስ ቢያንስ
የእኔ ካርድ ዝግጁ
ነው ፡፡
ቸር
እንሰንብት
በሁለተኛው ምርጫ ነክ
ጽሁፍ እስክንገናኝ
ሳምሶን
ብርሃኑ samsonbrh@gmail.com
|