የሁለት ሺህ ዓመቱ በዓልና የኤምባሲው ቅጥፈት! ( Pdf Click
here )
ዘነበ በቀለ
"ከሹመኛ ከባለፀጋ ሰው ጋር አትወዳጅ! አትሻረክ! የበደለህ እሱ ሲሆን አዙሮ አንተን
በደለኛ አድርጎ እንዳይበቀልህ" ይላል የጥንቶቹ ብልሆች ኢትዮጵያውያን ምክር። ምክራቸውን
የሰማው ተጠቅሞበታል። በተለያዩ ወቅቶችም በኪነጥበብ ፀጋው "ምንኛ ደግ ነው ከኩያ ጨዋታ
እሷ የኔ እመቤት እኔ የሷ ጌታ" በማለት በየቤተሰቡ ውስጥ ሳይቀር መመሪያው አድርጎት ሰላማዊ
ኑሮውን አራምዶበታል። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ "አቅምን አውቆ መኖር ጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ
ነው" የሚለው ዜማም በእያንዳንዱ ጆሮ እንዲያንቃጭል የሆነው ይህንኑ ሀቅ ለመመስከር ነው።
አለማችን በጥቅምና በአምሮት የተዋጠች በመሆኗ ያልሆኑትን ሆነው ለመታየት ወይም
በስሜት አብዶ ጨርቅን ለመጣል የሚጓጓው ሰው መለስ ብሎ እራሱን ለመፈተሽ የተሳነው መሆኑን
የምናስተውልበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ለመሆኑ አለም ምንድናት? የሰው ልጅሸ በኖረበት ዘመን
ሁሉ በሃብትና በገንዘብ አፍቅሮቱ ምንኛ ተደሳች ሆኖ አልፏል? በዓቅም መጠን ከመስራትና
ከማሰብ ይልቅ ያላቅሙ የሚወጠረው መንግስት ሁሉ በጥገኝነት እያገለገለ የተወላጆቹን ደም እንደ
ጎርፍ እያፈሰሰ መሆኑ እስከመቼ መቀጠል አለበት? ሞቱን የሚሞተው፤ እርሃቡን የሚራበው
አብዛኛው ደሃ ህዝብ እስከመቼ የናጠጡ ጥጋበኞች መናጆ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል? እስከመቼስ
በእብሪተኞች ተቀጥቅጦና ታስሮ በዚች አለም ላይ ለመኖር የተፈቀደለትን ጊዜውን በከንቱ ጨርሶ
ያልፋል? ወያኔ እንኳ በዓቅሙ ለማታለል ሙከራ አድርጓል። በአንድ ጀምበር ቱባ ቱባ ሀብታሞችን ሲፈጥር ለሁለት ጥቅም ብሎ መሆኑ ግልፅ ነው። አንድም በዚህ ተግባር ያሰለፋቸውን
ሁሉ "ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ" እንደተባለው እራሱ ወያኔ በሚፈፅመው ማናቸውም ወንጀል
ተጠያቂ ሆነው እንዲታዩ ለማድረግ ሲያዘጋጃቸው ሌሎችንም የዋሃን በጉጉት ስሜት
ጠፍሮ "ማነሽ ባለሳምንት." እባላለሁ በሚል ቅዠት ተውጠው ወንጀሉን በዝምታ እንዲመለከቱለት
ለማድረግ ነው። ይህ ዓይነቱ ነገር ቀደም ሲልም በሀገራችን በተደጋጋሚ የተስተዋለ ጉዳይ ነው።
አፄ ሀይለስላሴ እንዲያ የሚንከባከቧቸውን ሚኒስትሮቻቸውንና መኳንንቱን እንኳ በመጨረሻው
ሰዓት ከድተዋቸው ነበር። መንግስቱ ሀይለማርያም "ከሀቀኛው መሪያችን ጋር ወደፊት" እያሉ
ሲያጀጋንኑት የነበሩ የፓርቲ ጓዶኞቹን አስጠፍሮ ሸሽቷል። መለስ ዜናዊም ስልጣን ከወጣ በሁዋላ
የሜዳ ጓደኞቹን በሙሉ ዘብጥያ አውርዷል። አለያም አስገድሏል። ኤርትራን በማስገንጠል ሰላም
እናመጣለን እያለ ሲያቅራራ የነበረው መለስ ዜናዊ ከሽርካው ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር የከረረ
ጠብ ውስጥ ገብቶ ከሰባ ሺ በላይ የሆነ ንፁህ ህዝብ አስጨርሷል። ይኸ ከሀብትና ከዝና ጋር
የተያያዘ የጥቅም ሽኩቻ እንጂ ስለእኩልነትና ስለሀቅ፤ ስለሀገር ፍቅርና ስለህዝብ ብልፅግና
የተደረገ ግብግብ እንዳልሆነ ዛሬ ያ! ሲሰበክ የቆየው ህዝብ በሙሉ በተጨባጭ እያየው ነው።
የኢሳይያስ የነፃነት ጥያቄ ለኤርትራ ህዝብ ዳቦ አላስገኘም። የመለስም የሰላም ጩኸት
በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ውስጥ ገብቶ ወረራ እንዳያኬያሂድ አልከለከለውም። በዲሞክራሲ ስም
ያደረገው መሃላ ሁሉ እሱን ያልመረጠውን ህዝብ ከማሰቃየት ከመግደልና ከማሰር አላገደውም።
የቱ ነው እውነቱ? የቱ ነው ሀሰቱ? የምርቱ መትረፍረፍ ዜና ረሃብን አስወገደ ወይ? የከተሜው
መራብ የገጠሩ ህዝብ ጥጋብ ነው ከተባለ በገጠር ያለው ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ በልቶ ማደር
ችሏል ወይ? ይህንን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን አንስቶ ለራስ አጥጋቢ መልስ ማግኘት መቻል
ለድጋፍም ለተቃውሞም መሰረት ይሆናል።
የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በወያኔ ወኪሎች ተሞልተው የህዝቡን ሰቆቃ እንዳይታይ
ለማድረግ መጣራቸው አስገራሚ ባይሆንም ከዚህ በፊት ከህዝብ ጋር መቋም ተገቢ መሆኑን
አምነው የወያኔ ኤምባሲዎችን እየለቀቁ የወጡትን የህዝብ ልጆች ድምፅ መስማቱ ተገቢ በሆነ
ነበር። ይሁን እንጂ! በዚህ ፀረ ህዝብ በሆነ ድርጊታቸው ከገፉት መካከል የስቶክሆልሙ ኤምባሲ
አንዱ መሆኑን እያሳየን ነው። በቅርቡ ሀገር ቤት ለሚገኘው የወያኔ ቴሌቪዥን - ይህ ኤምባሲ
እንዳስተላለፈው በስካንዲኔቪያ አካባቢ ሚሌኒየሙን ለማክበር ኢትዮጵያዊው ማህበረሰብ
እየተንቀሳቀሰ ነው የሚል ቅጥፈት አክሎ ነበር። ይህ ቅጥፈት ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎችን
የሚያስነሳ ነው። በመጀመሪያ ወያኔ ሚሌኒዬሙን አከብራለሁ ብሎ የተነሳው በሀገር ውስጥ
በመሆኑ ባንድ መልኩ ካልገባችሁ እያለ ሲወተውት ይታያል። በሌላ መልኩ ደግሞ በውጭ
ያሉትን ኢትዮጵያውያን እንዲያከብሩ አሰባስቤአለሁ ይላል። ለነገሩ ባካባቢው ወያኔን ደግፎ
ሊንቀሳቀስ የተዘጋጀ ቡድን አልተመለከትንም። ደሞስ ወያኔ ለገንዘብ ስብሰባ ወይስ ለፖለቲካ
ማሳመሪያ ሚሊዬኔሙን አከብራለሁ ብሎ የሚመናተለው? በወያኔ ድርሳን ላይ ተፅፎ የሚገኘው
ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ ብቻ ነው ያላት የሚል ሆኖ ሳለ የቀረውን 1900 ዓመት ከየት
አመጣውና ነው የሁለት ሺ ዘመን ታሪክ ወያኔ ለማክበር የተነሳሳው? በስዊድን የሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ባብዛኛው የወያኔ ተቃዋሚዎች መሆናቸውን ሳይረዳው ቀርቶ ነው የወያኔ ኤምባሲ
ይህንን የመሰለ የሃሰት ወሬ ለማናፈስ የፈለገው? ወይስ ኢትዮጵያዊ ማለት የትግሬ ወያኔዎች ብቻ
ናቸው ብሎ አምኖ?
በአካባቢው እንደምናውቀው ከአስራ |