Kinijitswiss.org contact us
Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org Kinijitswiss.org
 


 
main content

 

የቁርጥ ቀን ጥሪ

ከሀገርህ ወተህ በልዩ ልዩ መልክ
ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአለም የተበተንክ
ግፍን ተጠይፈህ በደልና ስቃይ
እጫካ የገባህ ያለኸው ፍልሚያ ላይ
ባያስሩህም እንኳን በር ባይዘጉብህ
በሀገርህ ለመኖር ነጻነት ያሳጡህ
ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየትም ነዋሪ
ቀርቦልሀል ውጣ የቁርጥ ቀን ጥሪ
ወያኔ ኢህአዲግ የግፍ ስራው ብሷል
የጥፋትድርጊቱ አፍንጫ ስር ደርሷል
እስከዛሬ ድረስ ያሰራቸው ሳያንስ
መሪዎቻችንን በሀሰት በመክሰስ
ሀገር በማናወጥ ዘር በማጥፋት ወንጀል
ውሳኔ ሊሰጥ ነው ባልፈጸሙት በደል
በቅንጅት መንፈስ መሪው ሀይሉ ሻውል
ብርሀኑ ነጋ ሙሉነህ እዩኤል
ዶክተር ሀይሉ አርአያ ፕሮፌሰር መስፍን
ኢንጅነር ግዛቸው ዳኛዋ ብርቱካን
ዶክተር በፍቃዱ ያዕቆብ ኃ /ማርያም
ደበበ እሸቱና አቶ በድሩ አደም
ባገር ያበሩትን ተስፋ በማጨለም
እስር ቤት ወርውረው እውነትን በመካድ
ፍትህን ገንዘው መቃብር በማውረድ
ሰብአዊ መብትን እስከነ ቃላቱ
ስጋውን በመግፈፍ አቁመው በአጥንቱ
ህግንም እራሱን ጭለማ ቆልፈው
ግማሹን አፍነው ያሻቸውን ገድለው
ዲሞክራሲን ገፈው ከሀገር ትከሻ
አሳጥተውታል ህዝቡን መተንፈሻ
ይህንን እንዲአርም ከአለም ህብረተሰብ
ከሰላም ወዳዶች ብዙ ጥሪም ቢቀርብ
ማሰርን በመምረጥ ህግን ከለላ አድርጎ
ሊቀመጥ አስቧል አፍንጫ ሰንጎ
ስለዚህ ሁልህም አንድ ላይ በመሆን
የተበታተንከው ሳታብር እስካሁን
ጨርሶ እንዲአበቃ የሀሰት ውንጀላ
ባስቸኳይ እንዲለቅ ያሰረውን ሁላ
ምክንያት ሳትፈጥር ልዩ ልዩ ሰበብ
ይበቃልም ብለህ ትግልህን ሳትገድብ
ለሌላው አብርተህ ነደህ እንደሻማ
አገርህን አውጣ ከያዛት ጭለማ
እንዲሁም በቋንቋ በሀይማኖት በዘር
ልዩነት ሳይኖርህ አንድ ላይ በማበር
ዲሞክራሲ ሰፍኖ እንዲቆም በሀገር
ቀርቦልሀል ውጣ የቁርጥ ቀን ጥሪ
ለመሪዎቻችን ሆነህ ተቆርቋሪ

<< Back to previous page


 
`

@2007 - KINIJIT Support Organization In Switzerland Web Design By SaNet